Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ በእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በድሬዳዋ አሸዋ ገበያ በቅርቡ በደረሰ የእሳት አደጋ ምክንያት የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የ6 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእሳት አደጋው ባደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን ገልፀው ድጋፉን ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ከድር ጁሃር አስረክበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት ክልሉ የአደጋው ተጎጂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት በቀጣይም የሚደገፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ ከድር ጁሃር ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.