Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 163 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 163 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ዛሬ ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት ውስጥ 947 ወንዶች፣ 200 ሴቶች እና 16ቱ ጨቅላ ህፃናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች በአውሮፕላን ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ከሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ከ73 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል ነው የተባለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.