የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ጽሕፈት ቤቱን በኢትዮጵያ ከፈተ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ጽሕፈት ቤቱን በአንድነት ፓርክ ዛሬ አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢያሱ ወሰን እና የኮንፌዴሬሽኑ የቦርድ አባላትን ጨምሮ ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ጽሕፈት ቤት በኢትዮጵያ መከፈቱ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ለቦክስ ስፖርት እድገት ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባለፈም በስራ እድል ፈጠራ ያለው አስተዋጽኦ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡