Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በጤናው ዘርፍ የተያዙ ዕቅዶች እንዲሳኩ አመራሩ በቁርጠኝነት እንዲሠራ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ በቀጣዩ በጀት ዓመት የተያዙ ተገልጋይ ተኮር ዕቅዶችን ለማሳካት በየደረጃ ያለው አመራር በቁርጠኝነት እንዲሠራ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ አሳሰቡ፡፡

በድሬዳዋ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የጋራ መድረክ ተጠናቅቋል።

ዶ/ር መቅደስ በማጠቃላያው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ጥራቱ እና ፍትሐዊነቱ የተረጋገጠ አካታች የሆነ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ እንሠራለን ብለዋል።

ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረገ የጤና አገልግሎት ሥርዓትን በይበልጥ ለማስፋፋት እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡

ጤናን ማበልጸግ፣ በሽታን መከላከል እና የጤናው ዘርፍ ፋይናንስን በሚፈለገው ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸው÷ በተፈጥሮም ሆነ ሰው ሠራሽ የጤና አደጋዎችን ለመቋቋ የሚያስችል ዝግጅት እና ፈጣን ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓትም በትኩረት ይሠራበታል ነው ያሉት፡፡

በቀጣዩ የበጀት ዓመት የተያዙ ዕቅዶችን ለማሳካት የማሕበረሰቡን የነቃ ተሳትፎ በማጠናከር፣ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፣ በጤናው ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች፣ አጋር ድርጅቶች እና ባለድርሻ አካላት በትብብር መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.