Fana: At a Speed of Life!

በኮሪደር ልማት ስራ የተገኙ እምርታዎችን ቀምረን በሁሉም አካባቢዎች ተደራሽ እንዲሆኑ እንንቀሳቀሳለን – አቶ አደም ፋራህ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ውብ መንደሮች ኢትዮጵያ እንድትመስል የምንፈልገውን ብልፅግናዊ ምስል እየገለጡ ነው ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ፡፡

አቶ አደም ፋራህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የፓርቲያችን የከተማ ልማት እሳቤ በጠንካራ የስራ ባህል ተሟሽቶ፣ በህዝባችን ልማት ወዳድነት ከፍተኛ አቅም አግኝቶ፣ በሀገር በቀል የግንባታ ጠበብቶቻችን ድምር ውጤት ፍሬ አፍርቶ አዲስ አበባ ላይ ውጤቱን ፍንትው ብሎ አይተነዋል ብለዋል።

በኮሪደር ልማት አቧራን አራግፈን የገለጥነው ውበት፣ ከሰራን ሁሉም ሊለወጥ እንደሚችል ያረጋገጥነው እውነት፣ ዘወትር በትውልድ ልብ ውስጥ ተስፋ እና የይቻላል መንፈስን እንደሚጭር በፅኑ እናምናለንም ሲሉም ገልጸዋል።

የተገኘውን ውጤትም በአግባቡ በማጤን እና በቀጣይ በኮሪደር ልማት ስራ የተገኙ እምርታዎችን ቀምረን በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆኑ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥተን የምንንቀሳቀስ ይሆናል ሲሉም አክለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.