በዉይይት መድረኩ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር) ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አንተነህ ፍቃዱን ጨምሮ ሌሎችም የክልሉ አስተባባሪ አባላት እንዲሁም የፀጥታና ሠላም ግንባታ ቢሮ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዚህም የአመራር የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በማጠናከር ሠላምን፣ ልማትንና መልካም አስተደደርን የሚያጠናክር ፣ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያሻሸል ትግል እንዲጠናከር አቅጣጫ መቀመጡም ነው የተነገረው።
በሁለቱም መዋቅሮች የሚስተዋሉ የተዛቡ ፓለቲካዊ እሳቤዎችን፣ የመልካም አስተዳደርና የፀጥታ ችግሮችን በዝርዝር መገምገሙን ከክልሉ ኮሙኒኬን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም ችግሮቹ በዘላቂነት በሚፈቱበት ሁኔታ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱም ተመላክቷል፡፡