ወ/ሮ ሰመሪታ ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ሰመሪታ ሰዋሰው ከዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ (ኢፋድ) የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ሳራ ምባጎ ቡኑ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷በግሉ ዘርፍ ያሉ የሃብት ምንጮችን መፈለግና ከሌሎች የልማት አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ኢፋድ በኢትዮጵያ የገጠር ፋይናንስ ተቋማትን በማጠናከርና አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት የግብርና ልማት ላይ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተጠቅሷል፡፡
ውይይቱ በኢትዮጵያና ኢፋድ መካከል ያለውን አጋርነት በማጠናከር በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ ሚና ይኖረዋል መባሉን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡