የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የምርጫ ጊዜ 3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ÷የምክር ቤቱ አባላት ለመልካም አስተዳደር፣ ልማት፣ ፍትህ መረጋገጥ ኃላፊነታቸውን በትጋት ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በጉባኤው የክልሉ ምክር ቤት የመንግሥት አገልግሎቶች ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ሕጎችን እንደሚያወጣ ጠቁመዋል፡፡
ምክር ቤቱ አፈፃፀማቸውንም በመከታተል የአስፈጻሚ አካላት ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያፀድቅ አመላክተዋል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ ዛሬ በሚያካሂደው የአንድ ቀን መድረክ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ልዩ ልዩ አጀንዳዎች በማቅረብ ውሳኔ ይሰጥባቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡