Fana: At a Speed of Life!

የሐረሪ ክልልና የድሬዳዋ አስተዳደር አጀንዳዎችን የሚያደራጁ ወኪሎች መረጡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል እና የድሬዳዋ አስተዳደር የምክክር ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎችን የሚያደራጁ ወኪሎችን መርጠዋል፡፡

በሐረሪ ክልል እና በድሬዳዋ አስተዳደር የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍል ተወካዮች ከወከሉት ማህበረሰብ ይዘውት በመጡት አጀንዳ ላይ ሲወያዩ ቆይተዋል፡፡

በክልሉ ከትናንት ጀምሮ የባለድርሻ አካላት ወኪሎች አጀንዳዎቻቸውን በቡድን ካደራጁ በኋላ 30 ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎችን እንዲያደራጁ መርጠዋል፡፡

የተመረጡት የባለድርሻ አካላት ወኪሎች የክልሉን አጀንዳዎች የሚያጠናቅሩና የሚያደራጁ ይሆናል፡፡

ወኪሎቹ ያደራጇቸው አጀንዳዎች ነገ ለውይይት ቀርበው የክልሉ አጀንዳዎች ተደርገው ኮሚሽኑ የሚረከባቸው ይሆናል፡፡

እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከማህበራትና ተቋማት፣ ከመንግስት አስፈጻሚ አካላትና የታዋቂ ግለሰቦች ወኪሎች ጋር ሆነው የሚወያዩላቸውን 60 ወኪሎችን ዛሬ መርጠዋል፡፡

ወኪሎቹ ከነገ ጀምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሆነው በድሬዳዋ አስተዳደር አጀንዳዎች ላይ የሚመካከሩ ይሆናል፡፡

በቀጣይ ሶስት ቀናት አምስቱ ባለድርሻ አካላት የሚያደራጇቸው አጀንዳዎች በዋናው መድረክ ከቀረቡ በኋላ የድሬዳዋ አስተዳደር አጀንዳ ሆነው ኮሚሽኑ እንደሚረከባቸው ይጠበቃል፡፡

በፈትያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.