Fana: At a Speed of Life!

አቶ አሕመድ ሺዴ በጅቡቲ ኢነርጂ ሚኒስትር ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ በጅቡቲ ኢነርጂ ሚኒስትር ዮኒስ አሊ ገዲ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በጅቡቲ የሚገኘው ሆራይዘን ተርሚናል ለኢትዮጵያ ነዳጅ የመጫን አገልግሎትን በሚያጠናክረበት ጉዳይ ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡

ሆራይዘን ተርሚናል ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን አገልግሎት በማሳለጥና በማቀላጠፍ በነዳጅ ሥርጭቱ ላይ የሚፈጠረው መቆራረጥ እንዳይከሰትና ምንም ክፍተት ሳይኖር ተገቢ አገልግሎት መስጠት በሚቻልበት አገባብ ላይ መወያየታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

አዋሽ ዴፖን ከጅቡቲ ሆራይዘን ተርሚናል ጋር በባቡር ለማገናኘት በተደረገው ጥረት ተጓትተው የቆዩት ስምምነቶች በአስቸኳይ በሁለቱም ወገኖች በተሰየሙ ቴክኒክ ኮሚቴዎች ታይቶ ወደ ስምምነት በመድረስ በመጪው መስከረም ወር ውሉ ተፈርሞ ግንባታውን ለማስጀመር ከስምምነት መደረሱ ተጠቁሟል፡፡

በውይይቱ የሆራይዘን ተርሚናልና የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት የሥራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ አምባሳደር ግርማ ብሩና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ተሳትፈዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.