Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር የዘንድሮ ማዳበሪያ ማጓጓዝ ስራ ማጠናቀቁ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር የ2016 ዓ.ም የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ስራውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

266 ሺህ 770 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በ103 ባቡሮች በማጓጓዝ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው ሁሉ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገልጿል።

ለዚህም ስኬት አስተዋጽዖ ላበረከቱ አካላት ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ለቀጣዩ ዓመትም አፈጻጸሙን ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰራም ነው የጠቆመው፡፡

በዚህም ከነበረው የገበያ ድርሻ 14 በመቶ ወደ 20 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የማሳደግ ዕቅድ እንዳለው ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.