Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ግብርና የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፋኦ ጋር ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ግብርና የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፋኦ ጋር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መግባባት ላይ መደረሱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት(ፋኦ) ዋና ኢኮኖሚስት ማክሲሞ ቶሬሮ(ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱን አስመልክቶ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ ኢትዮጵያ የግብርና ስርዓቷን ለማዘመን እያደረገችው ባለው ጥረት የፋኦ የቴክኒክ እና የገንዘብ ድጋፍ ድርሻው ትልቅ እንደሆነ በምክክሩ መነሳቱን ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እና ያሉ ዕድሎችን ከመጠቀም አኳያ ከተቋሙ ጋር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከማክሲሞ ቶሬራ(ዶ/ር) ጋር መግባባት ላይ ደርሰናልም ነው ያሉት፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፋኦ ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ እያደረገ ላለው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በኢትዮጵያ መንግስት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.