Fana: At a Speed of Life!

በ3 የሆርቲካልቸር ምርቶች ላይ ከኮሜሳ ጋር በትብብር ለመሥራት ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በአቮካዶ፣ ቀይ ሽንኩርት እና ድንች ምርቶች ከምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ጋር በትብብር ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመች፡፡

የምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የሆርቲ ካልቸር ትስስር መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይም የደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ)፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ላኪዎች ማኅበር አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

መድረኩ የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር ምርቶችን በኮሜሳ ንግድ ቀጣና እንዲሁም በሌሎች የውጭ ገበያዎች ትስስር ለመፍጠር ያለመ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ከዚሀ ባለፈም በዘርፉ ተዋናዮች መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደሚያስችል በግብርና ሚኒስቴር የሆርቲካልቸር ዘርፍ ዋና ስራ አስፈጻሚ አብደላ ነጋሽ ተናግረዋል።

የተፈረመው ስምምነትም ምርቶቹን በቀጣናው ሀገራት እሴት ጨምሮ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ለማስቀረት ሚናው የጎላ መሆኑን በግብርና ሚኒስቴር የሆርቲካልቸር ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብደላ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያም በሆርቲካልቸር ዘርፍ በአበባ፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ እና ሌሎች ምርቶች ያላትን አቅም መጠቀም እንደሚገባ ገልጸው÷ በዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳሪነትንና የውጭ ምንዛሪ ገቢን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በትዕግስት አስማማው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.