የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በስኬት እንዲተገበር የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር የፍትሕና የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ አስገነዘቡ፡፡
ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ ወቅትም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር የፍትሕና የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ መሆኑን አስገንዝበው÷ ማሻሻያውን ለማደናቀፍ ሕግ የሚጥሱ አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው÷ ማሻሻያውን በተመለከተ የፖሊስ አመራሩ አስቀድሞ መረጃዎችን ማወቁ ለሕግ ማስከበር ሥራው ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል፡፡