Fana: At a Speed of Life!

 ኢትዮጵያ ከ12 ዓመት በኋላ በአትሌት አበባ አረጋዊ የነሐስ ሜዳሊያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2012 በለንደን በተካሄደው የአሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን በ1 ሺህ 500 ሜትር የወከለችው አትሌት አበባ አረጋዊ ከ12 ዓመት በኋላ ሜዳሊያዋን አግኝታለች።

አትሌቷ ከ12 ዓመት በፊት በለንደን በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ውድድር 5ኛ በመውጣት አጠናቃለች፡፡

ይሁን እንጂ በውጤቱ ተሳትፎ የነበራቸው ሌሎች አትሌቶች በተለያዩ ምክንያቶች በዓለም ዓቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ውጤታቸው እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡

ይህን ተከትሎም በወቅቱ 5ኛ ደረጃን ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌት አበባ አረጋዊ ደረጃዋ ወደ 3 ከፍ በማለቱ ከ12 ዓመታት በኋላ ለሀገሯ ያመጣችውን የነሀስ ሜዳሊያ ተረክባለች።

አትሌቷ ሜዳሊያውን በፓሪስ ኦሊምፒክ የመዝጊያ ስነ- ስርዓት ላይ ተገኝታ መውሰዷን ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.