የኩዌት ህዝባዊ የሰው ኃይል ኢትዮጵያውያን በኩዌት መስራት የሚችሉበትን ሁኔታ እያገዘ መሆኑን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኩዌት ህዝባዊ የሰው ኃይል ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እና ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን በኩዌት መስራት እንዲችሉ የሚደረገውን ጥረት ለማቀላጠፍ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።
በባለስልጣኑ የሰራተኛ ጉዳዮች ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሙሳድ አል ሙታሪ፣ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ መሀመድ እና የልዑካን ቡድናቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ተወያይተዋል።
አል ሙታሪ ሁሉም ሰራተኞች ለኩዌት ልማትና ሰብዓዊ ግቦች ከመንግስት ድርጅቶች እና ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
አምባሳደር ሰኢድ መሀመድ በበኩላቸው በውይይቱ፤ ባለስልጣናቱ ኢትዮጵያውያን በኩዌት መስራት እንዲችሉ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላደረጉት ጥረት አመስግነዋል፡፡
በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ መሆኑን መግለፃቸውን ኩዌት ታይምስ ዘግቧል።