Fana: At a Speed of Life!

የሕንድ የበጎ ፈቃድ ሕክምና ቡድን ነጻ ቀዶ ሕክምና መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕንድ የበጎ ፈቃድ ሕክምና ልዑካን ቡድን አባላት ለ10 ቀናት የሚቆየውን የነጻ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ጀምረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራቸውን የጀመሩት ባለሙያዎቹ  ሕክምናውን ለማድረግ  በሮተሪ ክለብ አማካይነት  መምጣታቸው ተገልጿል፡፡

በተለይ የዩሮሎጂ የቀዶ ሕክምና ተራ በመጠባበቅ  ላይ ላሉ፣ ከፍለው መታከም ለማይችሉና ወደ ውጭ ሀገር ሪፈራል ለሚያስፈልጋቸው ሕሙማን  አገልግሎቱን  እንደሚሰጡ ተጠቁሟል፡፡

የሐኪሞቹ ቡድን ለሕክምና አገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ድጋፍ እንዳደረገም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ  መረጃ ያመላክታል፡፡

በበጎ ፈቃድ ሕክምና መርሐ ግብሩ ከኮሌጁ ስፔሻሊስቶች ጋር  በትብብር የሚሠራ  ሲሆን÷ የእርስ በርስ የልምድ ልውውጥ እንደሚደረግም ተጠቅሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.