Fana: At a Speed of Life!

ዩክሬን በከርስክ 28 መንደሮችን መቆጣጠሯን ሩሲያ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዩክሬን በሩሲያ ከርስክ የሚገኙ 28 መንደሮችን ተቆጣጥራለች ስትል ሩሲያ አስታውቃለች፡፡

የከርስክ ተጠባባቂ ገዥ አሌክሲ ስሚርኖቭ ለሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ እንደገለጹት፤ ዩክሬን 28 የሩሲያ መንደሮችን መቆጣጠሯ አሳሳቢ ነው፡፡

የዩክሬን ጦር በቀጣናው ምን ያህል ዘልቆ እንደገባ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ሪፖርት እንደሚያደርግ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገልጸው፤ የከርስክ ገዥ በአካባቢው ያለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዜጎች ምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ እንዲገልጹላቸው ጠይቀዋል፡፡

በዚህም ስሚረኖቭ ለፑቲን በሰጡት ምላሽ 2 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በዩክሬን ቁጥጥር ስር ባለው አካባቢ እንዳሉ አብራርተዋል፡፡

በዚህም አሁን ያሉበትን ሁኔታ ማወቅ እንዳልተቻለ መግለጻቸውን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ፑቲን በበኩላቸው፥ ለድርጊቱ ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ በመግለጽ፥ አጸፋው ስኬታማ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።

እስካሁን ከከርስክ አካባቢ ከ76 ሺህ በላይ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው ወጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.