Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ በቀብሪ በያህ ከተማ ያስገነባቸውን ቤቶችና መማሪያ ክፍሎች አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በሶማሌ ክልል ቀብሪ በያህ ከተማ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ያስገነቧቸውን የአቅመ ደካማ ቤቶች እና የመማሪያ ክፍሎች ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል።

ሚኒስቴሩ ለመኖሪያ ቤቶቹና ለተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎቹ ግንባታ በአጠቃላይ 16 ሚሊየን ብር ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደተናገሩት÷ግንባታቸው የተጠናቀቁት ቤቶች በጥራትና በአነስተኛ ወጪ መገንባታቸውን ገልፀዋል፡፡

በክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች በመሳተፍ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን የመደገፉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ÷ሚኒስቴሩ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በክልሉ የቤትና የመማሪያ ክፍሎችን ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች በማስረከቡ አመስግነዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.