ኢትዮጵያ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ድል አልቀናትም
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ ባለው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ሳትገባ ቀርታለች።
በፓሪስ 2024 የኦሊምፒክ ውድድር ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ከ50 ላይ በተካሄደው የወንዶች 5 ሺህ ሜትር ፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት፣ አትሌት ቢኒያም መሐሪና አትሌት አዲሱ ይሁኔ ተሳትፈዋል።
በዚህም ሐጎስ ገብረሕይወት እና ቢኒያም መሐሪ አምስተኛና ስድስተኛ ደረጃ ይዘው ሲያጠናቅቁ፤ አዲሱ ይሁኔ 14ኛ ሆኖ ውድድሩን ጨርሷል።