Fana: At a Speed of Life!

ቀላል መለማመጃ አውሮፕላን ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር አውሮፕላኑ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ መገደዱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ በመደበኛው ስልጠና ልምምድ ላይ የነበረ ቀላል የተማሪዎች መለማመጃ አውሮፕላን ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር አውሮፕላኑ ነጌሌ አካባቢ ለማረፍ መገደዱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

የተፈጠረውን ችግር ተከትሎም የመለማመጃ አውሮፕላኑ ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች አንዲት ታዳጊ ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

የተፈጠረውን ችግር ተከትሎም የመለማመጃ አውሮፕላኑ ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ በማያደርስ ሁኔታ ለማሳረፍ ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም ለማረፍ በተደረገው ጥረት መሬት ላይ በነበረች ታዳጊ ላይ ጉዳት በማድረሱ የታዳጊዋ ህይወት ሊያልፍ ችሏል፤ በዚህም አየር መንገዱ ማዘኑን ገልጿል፡፡

የአደጋው መንስኤ በሚመለከታቸው አካላት በመጣራት ላይ መሆኑን ም አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ካጋራው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.