Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በኦሊምፒኩ የመጀመሪያ ወርቋን አገኘች 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ 2024  የኦሊምፒክ ወድድር በማራቶን ኢትዮጵያ በአትሌት ታምራት ቶላ አማካኝነት የመጀመሪያ ወርቋን አግኝታለች፡፡

በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች የማራቶች ውድድር የተካሄደ ሲሆን ÷አትሌት ታምራት ቶላ ፣ቀነኒሳ በቀለና ደሬሳ ገለታ ኢትዮጵያን ወክለው ተወዳድረዋል።

በዚህም ታምራት ቶላ ውድድሩን  2 ሰዓት ከ6 ደቂቃ ከ26 ሰከንድ በመግባት በቀዳሚነት በማጠናቀቅ በኦሊምፒኩ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል፡፡

አትሌት ደሬሳ ገለታ ደግሞ ውድድሩን በአምስተኛ ደረጃ  አጠናቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.