ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመከላከል የሚያስችል የፋይናንስ አገልገሎት ተቋማት የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
የውይይት መድረኩ “የፋይናንስ ደህንነነት አልግሎት የገንዘብ ዝውውርን እና ሌሎች የፋይናንስ ወንጀሎችን ለመከላከል የባንኮች ሚና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡
የፋናንስ አገልሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ በመድረኩ እንደተናገሩት ÷በተለይም ባንኮች ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን በመከላከል ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ ነው፡፡
በመድረኩ የብሄራዊ ባንክ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ባንኮች ተወካዮች እየተሳተፉ ሲሆን÷ለውይይቱ መነሻ የሚሆኑ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡
በሻምበል ምህረት