በሐረሪ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል ለሀገራዊ ምክክሩ ግብዓት የሚሆን አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ የመጀመሪያው ምዕራፍ መጀመሩን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት እንደሚከናወን እና1 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሳተፋበት መሆኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ተገኘወረቅ ጌጡ (ዶ/ር ) ገልጸዋል፡፡
አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ሁሉንም የክልሉን የህብረሰብ ክፍል ያማከሉ ወኪሎች ፣የመንግስት አካላት ተወካዮች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችም ጭምር የሚሳተፉበትና በነፃነት የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አጀንዳ የሚሰማበት መሆኑንም አንስተዋል።
አጀንዳ አሰባሰቡ ለዘመናት ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮቻችንን ለመፍታት አስቻይነት ያለው ነውም ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡
በፈቲያ አብደላና እዮናዳብ አንዷለም