በብራዚል በአውሮፕላን አደጋ የ62 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ On Aug 9, 2024 459 አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል ሳኦ ፖሎ ግዛት 58 መንገደኞችን እና አራት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ በህይወት የተረፈ ሰው አለመኖሩ ተገለጸ። ባለ መንታ ሞተር ቱርቦፕሮፕ አውሮፕላን በደቡብ ብራዚል ፓራና ከምትገኘው ካስካቬል ወደ ሳኦ ፖሎ ዋና አውሮፕላን ማረፊያ በመብረር ላይ ሳለ ቪንሄዶ ከተማ ሲደርስ ቁልቁል መውረዱን የቮፓስ አየር መንገድ ተናግሯል። ስለ አደጋው መንስኤ ለጊዜው የታወቀ ነገር ባይኖርም በአውሮፕላኑ ተሳፍረው የነበሩ በሙሉ ህይወታቸው ማለፉን ነው ቢቢሲ የዘገበው። 459 Share FacebookTwitterTelegramWhatsAppEmailViberPrint