Fana: At a Speed of Life!

ሠላምን በማጽናት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት ይሠራል- አቶ አሻድሊ ሃሰን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017 በጀት ዓመት የክልሉን ሠላም በማጽናት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሠራ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ÷በክልሉ የ2017 በጀት ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ላይ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

አቶ አሻድሊ ሃሰን በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ባለፉት ዓመታት የነበረው የጸጥታ ችግር በሁሉም ዘርፎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል።

ሠላምን በማጽናት በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አንስተዋል።

የኢንቨስትመንት ዘርፉን እንዲሁም የማዕድን ሃብት ሥራዎችን የበለጠ በማነቃቃት የክልሉን የገቢ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ መግለጻቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በበጀት ዓመቱ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ በሙሉ አቅም መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመው÷ ሁሉም የድርሻውን ሃላፊነት እንዲወጣ አሳስበዋል።

ለልማት ዕቅዱ መሳካት ጠንካራ የክትትል ሥራ እንደሚሠራም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.