Fana: At a Speed of Life!

 አትሌት ለሜቻ ግርማ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የ3 ሺህ መስናክል አትሌት ለሜቻ ግርማ ካጋጠመው ጉዳት አገግሞ በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

አትሌቱ ትናንት ምሽት በፈረንሳይ ፓሪስ ኦሊምፒክ በተካሄደው የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል ውድድር በመጨረሻ ዙር የመሰናከሉ ጠልፎት በመውደቁ ጉዳት ማስተናገዱ ይታወሳል፡፡

በዚህም ወደ ሆስፒታል ገብቶ በተደረገለት ምርመራ በእግሩና በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት እንዳልደረበሰት የህክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል።

የአትሌት ለሜቻ ግርማ አሰልጣኝ ተሾመ ከበደን ዋቢ አድርጎ ያሁ ኒውስ እንደዘገበው፤ አትሌቱ በዛሬው እለት  ከሆስፒታል ወጥቶ ወደ ኦሊምፒክ መኖሪያ መንደሩ መመለሱ ተገልጿል፡፡

የ3 ሺህ መሰናክል ባለሪከርዱ ለሜቻ ግርማ በኦሊምፒኩ የወርቅ አሸናፊነት ግምት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም አጨራረስ ላይ ያጋጠመውን ጉዳት ተከትሎ ሞሮኳዊው የመሰናክል ተፎካካሪው ሶፊያን ኤል ባካሊ አሸንፏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.