አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከግብፅ አምባሳደር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በኢትዮጵያ ከግብፅ አምባሳደር መሀመድ ኦማር ጋድ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ÷በሁለትዮሽ፣ቀጠናዊ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸውና በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ እንዲሁም አልሸባብ በሶማሊያና በቀጣናው ባሳድረዉ ስጋት ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም ውይይቱ በድህረ-አትሚስ ተልዕኮ እና በኢትዮጵያ ፍላጎቶች ላይ ያተኮረ እንደነበር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡