የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በደሴ ከተማ የገነባው የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በጽሕፈት ቤታቸው ወጪ በደሴ ከተማ የተገነባውን የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካ መረቁ፡፡
ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦ እና 420 ኩንታል ዱቄት የማምረት አቅም አለው መባሉን የጽሕፈት ቤቱ መረጃ አመላክቷል፡፡
የዳቦ እና ዱቄት ፋብሪካው በጽሕፈት ቤቱ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት መሰረት በማድረግ እየተተገበሩ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ መሆኑም ተገልጿል፡፡