በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ማጣሪያ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ግማሽ ፍጻሜ አለፉ።
ዛሬ ረፋድ 5 ሠዓት ከ5 ላይ በተካሄደው 1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይና ድርቤ ወልተጂ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል።
በዚህም ጉዳፍ ጸጋዬ 3:58.84 በሆነ ሰዓት፤ ድርቤ ወልተጂ ደግሞ 3፡59.73 በሆነ ሰዓት በመግባት ከምድብ አንድ እና ሁለት ማጣሪያውን በቀዳሚነት አጠናቅቀዋል፡፡