Fana: At a Speed of Life!

በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ የማቋቋም ሥራ ይሰራል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ የማቋቋም ሥራ ይሰራል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡

የክልሉ የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤት በክልሉ የአደጋ ተጋላጭነት፣ ዝግጁነት እና ምላሽ አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

በክልሉ በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎችን በአጭር ጊዜ የማቋቋም ሥራ በተቀናጀ መልኩ እንደሚከናወን የምክር ቤቱ ሰብሳቢና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች የዕለት ተደራሽ ሰብዓዊ ድጋፍ ከማቅረብ ባሻገር በአጭር ጊዜ የመኖሪያ ቤት በመስራት ለማቋቋም እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡

የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው÷በክልሉ ለሚከሰቱ አደጋዎች በአከባቢው ያሉ ሃብቶችን በማቀናጀት ፈጣን ምላሽ መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በክልሉ የአደጋ ክስተት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና በዚህም በተለያየ ደረጃ የሚገለጽ ጉዳት መድረሱን የገለጹት ደግሞ የክልሉ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለማ መሰለ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

በክልሉ የሚከሰቱ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮ አደጋዎችን በራስ አቅም ለመቋቋም በተሰጠው አቅጣጫ አንዳንድ የክልሉ ዞኖች ሃብት ማሰባሰብና ተጠባባቂ ምርት ማምረት መጀመራቸውን እንደገለጹም የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.