ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት የ5 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓሪስ እያስተናገደችው በሚገኘው 33ኛው ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ የምትጠበቅበት 5 ሺህ ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ከ15 ላይ ይካሄዳል፡፡
በዚሁ የፍጻሜ ውድድር ኢትዮጵያን በመወከል አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ፡፡
እንዲሁም ምሽት 4 ሠዓት ከ47 ላይ በሚካሄደው የ800 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ እና ወርቅነሽ መለሰ ይጠበቃሉ፡፡
በተጨማሪም ምሽት 2 ሠዓት ከ4 ላይ የ3 ሺህ ሜትር ወንዶች መሰናክል የማጣሪያ ውድድር ይካሄዳል፡፡
በዚሁ ርቀት አትሌት ለሜቻ ግርማ፣ ጌትነት ዋለ እና ሳሙኤል ፍሬው ይሳተፋሉ።