Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል የሕብረተሰብ ተወካዮች አጀንዳቸውን ለይተው ለኮሚሽኑ አስረከቡ

 

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ቀናት በጋምቤላ ክልል ሲካሄድ የቆየው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ መርሐ ግብር በዛሬው ዕለት ተጠናቅቋል፡፡

ከሐምሌ 22 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ከ14 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች አጀንዳቸውን አጠናክረው ለመረጧቸው 60 ተወካዮች ማስረከባቸው ይታወሳል።

ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ደግሞ የክልል ባለድርሻዎች ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሲቪክ ማህበራት፣ከታዋቂ ግለሰቦችና የማህበረሰቡ ተወካይ የሆኑ 60 ሰዎችን ያማከለው የአጀንዳ ማሰባሰብ ትናንት አጀንዳቸውን የሚያደራጁላቸው 25 ሰዎችን መርጠው አጀንዳቸውን ሲያደራጁ ቆይተዋል።

ዛሬም የተመረጡት 25 ተወካዮች የክልሉን አጀንዳ በማደራጀት ለጉባዔው አቅርበው ከተነበበና ከተሰማ በኋላ ለኮሚሽኑ አስረክበዋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም እንዳሉት÷ በጋምቤላ ክልል ሲካሄድ የነበረው የአጀንዳ ማሰባሰብ፣ የውይይት መድረክና የሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ተሳታፊዎች ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል።

አጠቃላይ በክልሉ የተካሄደው መድረክ የሚያኮራና ውጤታማ ሥራዎች የተከናወኑበት እንደነበር አስታውቀዋል።

የጋምቤላ ክልል ምክክር ተሳታፊዎች ያስረከቧቸውን አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክር ቤት ቀርበው ለመጨረሻው ሀገራዊ ጉባዔ እንዲቀርቡ ይደረጋልም ብለዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.