ፓርቲው የፌደራል ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት አስተባባሪ ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
በመርሐ-ግብሩ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት ሱፐርቪዥን ሪፓርት ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት እንደሚገኝ ከጽ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የፌደራል ተቋማት አደረጃጀት በበጀት ዓመቱ የተገኙ መልካም ልምዶችን አቅም አድርጎ ለማስቀጠልና የተስተዋሉ ክፍተቶችን ደግሞ በቀጣይ ለማስተካከል በዝርዝር እንደሚገመገምም ነው የተገለጸው፡፡