ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተሟላ መሠረተ-ልማት እንደተገነባላቸው አረጋግጠናል – ቻይናውያን ባለሀብቶች
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዱስትሪ ፓርኮች የተመለከትናቸው መሰረተ ልማቶች ለትርፋማ ኢንቨስትመንት መሰረት ናቸው ሲሉ የቻይና ከፍተኛ የመንግሥትና የቢዝነስ ልዑካ አባላት ገለጹ፡፡
ከቻይና የተለያዩ ግዛቶች የመጡ ከ90 በላይ የልዑኩ አባላት የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሥራ እንቅስቃሴንና አጠቃላይ የምርት ሂደትን ጎብኝተዋል።
በዚሁ ወቅትም በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችና የመሠረተ-ልማት አቅርቦቶች ለኢንቨስትመንት ምቹ እና ለአትራፊነትም መሠረት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ገብተው ለመሥራት የቅድመ ኢንቨስትመንት ተግባር እንደሚያከናውኑም ገልጸዋል።