Fana: At a Speed of Life!

ሠላምን ለማፅናት ርብርብ ሲደረግ ሌሎች ዕቅዶች በሚፈለገው ልክ አልተፈጸሙም – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላምና ጸጥታ ሥራን ለማስተካከል በወሰድነው ጊዜ ክልሉ ያቀዳቸውን ሌሎች ተግባራት በሚፈለገው ልክ አልፈጸመም ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ገለፁ፡፡

የክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በመድረኩ ላይ ባደረጉትንግግር በ2016 ክልሉ የነበረበት የሰላም ችግር የታቀደውን የልማት ግብ እውን እንዳይሆን አድርጎታል ብለዋል፡፡

ያለፈው ችግር ጥላውን እንዳያጠላም የቀጣዩን በጀት ዓመት ዕቅድ ከፍ ላለ አፈጻጸም የምንዘጋጅበት ነው ብለዋል።

ሰላምን በማጽናት እና በ2016 ዓ.ም ያልፈጸምናቸውን ከቀጣዩ ዓመት ዕቅድ ጋር በማናበብ በሚፈለገው ልክ ለመፈጸምም በቅንጅት መሥራት ግድ ይለናል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ክልሉን በተለያየ መስክ ለማሳደግና ከ2018 እስከ 2022 ዓ.ም የሚተገበር ፍኖተ-ካርታ ተዘጋጅቶ በየደረጃው ላለው አመራር ለውይይት መቅረቡንም አስታውቀዋል፡፡

ዕቅዱ በክልሉ በማክሮ ደረጃ የሚታዩ ችግሮችንና ጥንካሬዎችን በመተንተን መዘጋጀቱን ጠቅሰው÷ ከነበርንበት የሰላም ችግር ወጥተን የተዘጋጀ ዕቅድ በመሆኑ በቁጭት ሰርተን የምናሳይበት ነው ብለዋል፡፡

በፍሬሕይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.