Fana: At a Speed of Life!

በኦሊምፒክ ውድድሮች የኢትዮጵያ ተሳትፎ ዕድገት

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የዘንድሮውን ጨምሮ በታሪኳ በ15 የኦሊምፒክ ውድድሮች ተሳትፋለች፡፡

የመጀመሪያ ተሳትፎዋ በሆነው 16ኛው የኦሊምፒክ ውድድር 12 አትሌቶችን ያሳተፈቸው ኢትዮጵያ÷ በአትሌቲክስ (ዱላ ቅብብልን ጨምሮ) እና በብስክሌት ውድድሮች ተካፍላለች፡፡

በ17ኛው የኦሊምፒክ ውድድርም በ10 ስፖርተኞች በአትሌቲክስና በብስክሌት ዘርፍ ተሳትፋለች፡፡

እንዲሁም በአትሌቲክስ፣ ቦክስና ብስክሌት ስፖርቶች 12 አትሌቶችን በመያዝ በ18ኛው ኦሊምፒክ ውድድር መካፈል ችላለች፡፡

በ19ኛው የኦሊምፒክ ውድድሮችም በ18 ስፖርተኞች በአትሌቲክስ፣ ቦክስና ብስክሌት የስፖርት ዓይነቶች ተሳትፋለች።

በ20ኛው የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ፣ ቦክስና ብስክሌት 31 ስፖርተኞችን ይዛ ቀርባለች።

ኢትዮጵያ 45 አትሌቶችን በአትሌቲክስ፣ ቦክስና ብስክሌት ስፖርቶች ያሳተፈችው በ22ኛው የኦሊምፒክ ውድድሮች ላይ ነው፡፡ ይህም በታሪኳ በርካታ ተወዳዳሪዎችን ያሳተፈችበት ወቅት ነው፡፡

በ25ኛው የኦሊምፒክ ውድድር በአትሌቲክስና በብስክሌት 20 ስፖርተኞችን አሳትፋለች።

እንዲሁም በ26ኛው የኦሊምፒክ ውድድር 18 ስፖርተኞችን በአትሌቲክስና ቦክስ ስፖርቶች አሳትፋለች።

በ27ኛውን የኦሊምፒክ ውድድርም ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ቦክስ 26 ተወዳዳሪዎችን ይዛ መቅረቧ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል በ28ኛው የኦሊምፒክ ውድድር ላይ ኢትዮጵያ በአትሌቲክስና ቦክስ 26 ስፖርተኞችን አሳትፋለች።

በአትሌቲክስ ዘርፍ ብቻ በተሳተፈችበት 29ኛው የኦሊምፒክ ውድድርም 27 ተወዳዳሪዎችን ይዛ ተካፍላለች፡፡

12ኛ ተሳትፎዋ በሆነው 30ኛው የኦሊምፒክ ውድድር ደግሞ 35 ስፖርተኞችን በአትሌቲክስና በውሃ ዋና ስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ አሳትፋለች።

በ31ኛው የኦሊምፒክ ውድድር ደግሞ በአትሌቲክስ፣ ብስክሌትና ውሃና ዋና ስፖርቶች ተሳትፋለች።

በአራት ስፖርቶች 38 ስፖርተኞችን ባሳተፈችበት 32ኛው የኦሊምፒክ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በቴኳንዶ ተካፍላለች፡፡ በተጨማሪም አትሌቲክስ፣ ብስክሌት እና ውሃ ዋና ይገኙበታል፡፡

በፈረንሳይ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው በዘንድሮው 33ኛ የኦሊምፒክ ውድድር ኢትዮጵያን ጨምሮ 206 ሀገራት እና 10 ሺህ 500 ስፖርተኞች በ32 የስፖርት ዓይነቶች ይወዳደራሉ።

ኢትዮጵያም በ15ኛ የውድድሩ ተሳትፎዋ በአትሌቲክስና ውሃ ዋና ስፖርቶች 38 ስፖርተኞችን እያሳተፈች ነው፡፡

መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ!!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.