በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ 399 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 848 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 399 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች 398 ኢትዮጵያውያን እና አንዱ የውጪ ሀገር ዜጋ ሲሆን ÷ከ4 እስከ 85 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙ ናቸው ተብሏል።
ከዚህ ውስጥ 195 ወንዶች እና 204 ሴቶች ናቸው።
135 ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ለይቶ ማቆያ፣132 ሰዎች ከደዎሌና ጋሊሌ ለይቶ ማቆያ፣ 86 አዲስ አበባ፣ 9 ኦሮሚያ ክልል፣ 1 ደቡብ ክልል፣ 1 ጋምቤላ ክልል፣ 18 አማራ ክልል፣ 2 ትግራይ ክልል፣ 14 ድሬዳዋ እንዲሁም ከሶማሊያ ክልል 1 ሰው ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በተያያዘ በትናንትናው እለት የ95 ሰዎች (82 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከአማራ ፣ 2 ከሶማሌ፣ 1 ከትግራይ፣ 1 ከኦሮሚያ እንዲሁም 1 ከጋምቤላክልል) ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 122 ደርሷል ነው የተባለው።
እስካሁን በኢትዮጵያ ለ211 ሺህ 871 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሺህ 469 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።