Fana: At a Speed of Life!

“እንሥራ” የሸክላ ስራ ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) “እንሥራ” የሸክላ ስራ ማዕከል የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት ተመረቀ።

የማዕከሉ ግንባታ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ መሆኑ ተገልጿል።

በማዕከሉ 1 ሺህ በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ እና ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር ያገኛሉ ተብሏል።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዚህ ወቅት የሸክላ ስራ የሙያውን ያህል ያልተከበረ የድካሙን ያህል ጥቅም ያልተገኘበት ሆኖ መቆየቱን ተናግረዋል።

አያይዘውም የከተማ አስተዳደሩ ዘርፉን ባለሙያዎችን በሚያሳድግና ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ለማሳደግ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

የሸክላ ምርቶቹ ከሀገር ውስጥ ገበያ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ገበያ እንዲያገኙ ከተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ንግግር እየተደረገ መሆኑንም አንስተዋል።

ዘርፉን የሚደግፉ የህግ ማሻሻያዎች እየተዘጋጁ ነው ማለታቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በከተማዋ ከሸክላ ስራ ማዕከሉ በተጨማሪ የሸማ ጥበብ ማምረቻና መሸጫ ማዕከል ሽሮ ሜዳ አካባቢ እየተገነባ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.