Fana: At a Speed of Life!

አማራ ክልል ከ41 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2016 የበጀት ዓመት ከ41 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ክብረት ማሕሙድ አስታወቁ፡፡

ከ2015 ተመሳሳይ ወቅት አንጻርም አፈጻጸሙ ከ3 ነጥብ 18 ቢሊየን ብር በላይ እድገት ማሳየቱን ጠቅሰዋል፡፡

ዕቅዱን ለማሳካት አዳዲስ ግብር ከፋዮችን መመዝገብን ጨምሮ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ማለታቸውን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል በክልሉ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ ችግር፣ የሐሰተኛ ደረሰኝ መበራከት፣ ደረሰኝ ያለመቁረጥ ፣ ታክስ ማጭበርበርን ጨምሮ ሌሎች ተግዳሮቶች ከዚህ በላይ መፈጸም እንዳይቻል ዕክል መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.