Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለያዩ የልማት ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን ርዕሰ መሥተዳድር አወል አርባ ገለጹ፡፡

የክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 3ኛ የሥራ ዘመን፣ 6ኛ መደበኛ ጉባዔውን በሠመራ ከተማ እያካሄደ ነው።

ክልሉ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት የተመዘገበባቸው ተግባራት ማከናወኑን ርዕሰ መሥተዳድሩ በጉባዔው ላይ ባቀረቡት ሪፖርት አመላክተዋል፡፡

ለአብነትም በግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትና በመንገድ ጥሩ አፈጻጸም ተመዝግቧል ብለዋል።

ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከርም የተለያየ ሥራ መሠራቱን ጠቅሰው÷ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት መደረጉን አስታውቀዋል።

ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ከመከላከል አንጻርም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ክልሉን አቋርጠው ወደ ጎረቤት ሀገር ሊወጡ የነበሩ 9 ሺህ 773 ሰዎች ወደመጡበት አካባቢ እንዲመለሱ መደረጉን አንስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በዚህ ተግባር የተሰማሩ 13 ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችም በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.