Fana: At a Speed of Life!

 በኮምቦልቻ አረንጓዴ ዐሻራ የማኖርና የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሠራተኞች በኮምቦልቻ ከተማ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር አካል ችግኝ ተክለዋል፡፡

በተጨማሪም የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት እና የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ላለባቸው ተማሪዎች የሚሆን የቦርሳ፣ ደብተርና እስክብሪቶ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል፡፡

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት÷  መርሐ-ግብሩ የዲጂታልና የግሪን ኢኮኖሚ ግንባታን በማስተሳሰር ማኅበረሰቡን የአረንጓዴ ልማት ባለቤት ለማድረግ ያለመ ነው፡፡

ኮምቦልቻና አካባቢው ትልቅ የፍራፍሬ ኮሪደር የመሆን  አቅም እንዳለው ገልጸው÷ አካባቢውን ከማስዋብ ባለፈ ፍሬያቸው ለምግብነት የሚወሉ ችግኞችን ታሳቢ ያደረገ የግሪን ኢኮኖሚ ግንባታ ሊሠራ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡

ኮምቦልቻ በ2017 ዲጅታላይዝ ለማድረግ ከተመረጡ ከተሞች አንዷ ናት ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን በበኩላቸው ÷ ከአረንጓዴ ልማቱ ተጠቃሚ የሚሆን ማኅበረሰብ ለመፍጠር እና ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት መንግሥት እየሠራ  መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.