Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ ንግድና ፋይናንስ ግሩፕ ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከተለያዩ ሀገራት ከተውጣጡ የዓለም አቀፍ ንግድና ፋይናንስ ግሩፕ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የዓለም አቀፍ ንግድና ፋይናንስ ግሩፕ ፕሬዚዳንትና ዋና ስራ አስፈያፃሚ ኬ ጂ ሊ ፈርመዋል፡፡

ስምምነቱ ታዳሽ ኢነርጂ የሚጠቀሙ ተሽከከርካሪዎችን በመገጣጠም እና በማምረት ስራ ላይ የሚሰማሩ ባለሀብቶችን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት እንደሚያስችል ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

በተጨማሪም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እንዲሁም በትራፊክ እና የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ተስማምተናል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ዘርፍ መሰማራት አዋጪ መሆኑንም አመልክተው፤ መንግስት ምቹ ፖሊሲዎችን መዘርጋቱን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ የሰው ሀይል የሚገኝባት፣ ለኢንቨስትመንት ምቹና በኢኮኖሚም በፈጣን ሁኔታ እያደገች ያለች ሀገር በመሆኗ የግል ባለሀብቶች እንደሚመርጧት አስገንዝበዋል።

ኬ ጂ ሊም በበኩላቸው፤ በዘርፉ በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈጸማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ ዕድል ለመፍጠር፣ ጽዱና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገርን ለመፍጠር በጋራ እንሰራለን ብለዋል፡፡

የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠትም የሰው ሃይል ልማቱ ላይ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በዘቢብ ተክላይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.