የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት የአረንጓዴ ስምምነት ልዑክ ቡድን መሪ ሮቤርቶ ስኪሊሮ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም፤ የቡና ምርትን እሴት ሰንሰለት ለማሳደግና የውጭ ገበያ አማራጮችን ለማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በኢኮኖሚና ሌሎች ጉዳዮች በትብብር እየሰሩ የሚገኙት ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት፤ በተለይ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በትብብር እየሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ቡና በህብረቱ አባል ሀገራት ገበያ በስፋት ለማቅረብ ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት በጋራ እየሰሩ ሲሆን፤ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
የቡና የአቅርቦቱና እሴት ሰንሰለቱ ከአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ነጻ ደንብ ጋር መጣጣም እንዳለበት መገለጹን የግብርና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።