Fana: At a Speed of Life!

 የፓሪስ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በፓሪስ መካሄድ የሚጀምረው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ ስርዓት መካሄድ ጀምሯል።

የኦሊምፒክ መክፈቻ ስነ ስርዓቱ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስታዲየም ውጪ በሴይን ወንዝ ላይ የመርከብ ጉዞ በማድረግ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መረጃ እንደሚያመለክተው ከ203 ሀገራት የተወጣጡ 10 ሺህ 500 አትሌቶች በ32 የስፖርት አይነቶች ይወዳደራሉ።

ከሀገራቱ በተጨማሪ በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥላ ስር ገለልተኛ አትሌቶችና የኦሊምፒክ የስደተኞች ቡድን ይሳተፋሉ።

በ39 ስፖርተኞች የምትወከለው ኢትዮጵያ በዋናነት በተለያዩ ርቀቶች በሚደረጉ የሩጫ ውድድሮች ትካፈላለች።

ፈረንሳይ የዘንድሮውን የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ለማስተናገድ 9 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንዳደረገች መረጃዎች ያመለክታሉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.