የሶማሊ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሶማሊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤ በዛሬው እለት ተጠናቅቋል።
ጉባኤው በዛሬ ውሎው የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት፣ የክልሉ የብዙሃን መገናኛ ኤጀንሲ እና የሶማሊ ክልል ዋና ኦዲተር ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርትን አዳምጡ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን አፅድቋል።
ምክር ቤቱ የቀረበለትን የካቢኔ አባላትን ሹመት በአብላጫ ድምፅ በማፅደቅ ጉባኤውን ማጠናቀቁን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።