Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ጉባዔውን አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ምርጫ ጊዜ 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ የተለያዩ ሹመቶችን እና የአመራር ሽግሽግ በማጽደቅ ተጠናቋል።

በዚሁ መሰረት አቶ ቻም ኡቦንግ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ባጓል ጆክ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ቱት ጆክ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ፣ አቶ ገላዊት ታኒጌሳን የግብርና ቆላማ አካባቢ ልማት የተፈጥሮ ሃብት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንዲሁም ወ/ሮ አለሚቱ አለባቸው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው በመሾም ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረበለትን የዘጠኝ ዳኞች ሹመትን መርምሮ አፅድቋል።

እንዲሁም በምርጫ ውክልና አግኝተው ለመረጣቸው ሕዝብ ቀርበው ማገልገል ያልቻሉትን ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሁለት ጉባኤ አባልትን ውክልና አንስቷል።

የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ባንቻየሁ ድንገታ÷ የክልሉን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን በማሳካት ሕዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሩ በትጋት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

በአዲሱ በጀት ዓመት በ2016 የተገኙትን መልካም ተሞክሮች በማስፋት የሕዝቡ የልማት ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ምክር ቤቱ የክትትልና ድጋፍ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.