Fana: At a Speed of Life!

የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የተከበረው የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ-ንግስ ያለፀጥታ ችግር ተከብሮ መጠናቀቁን የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች የጋራ ፀጥታ ግብረ-ኃይል ገለጸ።

በዓሉ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የተቀናጀ ተግባር ሲከናወን መቆየቱ ተገልጿል።

በዚህም የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ምሥራቅ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የድሬዳዋ ፖሊስ፣ የምስራቅና ምዕራብ ሐረርጌ ፖሊስ፣ የሐረሪ ክልል ፖሊስ፣ የምስራቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ እንዲሁም የሚሊሻ ኃይሉ ጋር የጋራ ዕቅድ በማውጣትና ከቤተክርስቲያኗ አባቶች ጋር በመምከር ሰፊ ስራ መስራታቸው ተነግሯል።

በመሆኑም ክብረ በዓሉ ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በድምቀት ተከብሮ መጠናቀቁን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ አመልክቷል።

በዓሉን ለማክበር በመጡ ምዕመናን ላይ አንዳንድ የሞባይል ስርቆት ወንጀል በፈፀሙ አካላት ላይ በተቋቋመው ፈጣን ችሎት አማካኝነት ከ1 ዓመት ከ2 ወር እስከ 1 አመት ከ8 ወር የሚደርስ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.