Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ በተገኙ ስኬቶች ሳይዘናጋ ለተሻለ ውጤት ሊረባረብ ይገባል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በየደረጃው ያለው አመራር በተገኙ ስኬቶች ሳይዘናጋ ለተሻለ ውጤትና ለውጥ መረባረብ እንዳለበት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አሳሰቡ።

የኦሮሚያ ክልል ላለፉት ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ላይ ያተኮረ ውይይት አጠናቅቋል።

በማጠናቀቂያ መርሐ ግብሩ ላይ በሰላምና ፀጥታ፣ በልማት ስራዎች፣ በአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ማስፈን የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ በየደረጃው ላሉ የአስተዳደር መዋቅሮች እውቅና ተሰጥቷል።

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በውቅቱ እንደተናገሩት፤ በተያዘው በጀት ዓመት የተያዙ እቅዶችን ለማሳካት የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ትኩረት ሊደረግ ይገባል።

አመራሩ በተገኘው ውጤት ሳይዘናጋ እቅዱን ለመፈጸም ከወዲሁ በትኩረት መስራት እንዳለበት ገልጸው÷ ክፍተቶችን በማስተካከል ሁሉም አመራር በሙሉ ዓቅም ወደ ስራ መግባት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ ዕውቅና የተሰጣቸው ቀበሌዎች፣ ወረዳዎች፣ ከተሞች፣ ዞኖችና የክልሉ ተቋማት የቤት ስራቸውን በተሻለ ደረጃ በመፈፀም ምሳሌነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

በሁሉም የልማት መስኮች አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ መገለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.