የብሪክስ የንግድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ውይይት እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪክስ የንግድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት “በአዲሱ የዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ስርዓት ውስጥ የብሪክስ ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
በሩሲያ ሞስኮ እየተካሄደ በሚገኝው የንግድ ሚኒስትሮች ጉባኤ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እየተሳተፉ ነው፡፡
ውይይቱ በዓለም አቀፍ ፖለቲካ መድረክ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የብሪክስ ሚና በንግድና ኢኮኖሚ ረገድ እየጠነከረ የመጣውን የብሪክስ አባል ሀገራት ትብብር ለማጎልበት የሚያግዝ መሆኑን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን ለመቋቋም እና በዓለም ንግድ ድርጅትና ሌሎች ዓለም አቀፋዊ አደረጃጀቶች የጋራ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ ውይይቱ ሰፊ ጠቀሜታ እንዳለው መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።